ኢንፊኒቲ ለሠራተኞቹ በማርኬቲንግ እና የለውጥ ተግባራት ዙሪያ ስልጠና ሠጠ።

ኢንፊኒቲ ለሠራተኞቹ በማርኬቲንግ እና የለውጥ ተግባራት ዙሪያ ስልጠና ሠጠ።
ኢንፊኒቲ ለሠራተኞቹ በማርኬቲንግ እና የለውጥ ተግባራት ዙሪያ ስልጠና ሠጠ።

ማኅበሩ በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበ የሚገኝ ሀገራዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማኀበር ነው። ለዚህ ውጤት ድግሞ በተደራጀ እና የላቀ ሙያ እና ብቃት ባለው ማኔጅመንት እና ሠራተኛ መመራቱ ነው።

ማኀበሩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሠጠው ስልጠና ደንበኛ ተኮር በሆኑ የማርኬቲንግ ጽንሰ ሀሳብና ተግባር እንዲሁም በውጤታማነት የለውጥ ተግባራት ዙሪያ ያተኮረ ነው።

የማኅበሩ ህልውና የሆኑትን የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎት መስጠት ዋናው የትኩረት አቅጣጫ ነው። ማኀበሩ ለሠራተኞቹ በየጊዜው አቅማቸውን ለማጎልበት በዘመናዊ አሠራሮችና ቴክኖሎጅዎች እንዲሁም በአገልግሎት አሠጣጥ መሻሻል ዙሪያ ሥልጠናዎችን ይሠጣል።

ኢንፊኒቲ ከንብ ባንክ ጋር በመተባበር የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጅን ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ኢንፊኒቲ ለቤት፣ ለመኪና፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለልጆች፣ ለወጣቶች እንዲሁም ለተለያዩ የህብረተሠብ ክፍሎች የረጅም ጊዜ እንዲሁም ሳምንታዊ ብድር በማቅረብ ተመራጭ የፋይናንስ ተቋም ሆኗል።

ማኀበሩ በወለድም ይሁን የሸሪአ ህግን በተከተለ የወለድ አልባ አገልግሎት ለደንበኞቹ የተሻለ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለመስጠት እየተጋ ይገኛል። አገልግሎቱን በማስፋትና ሀገራዊ ተደራሽነቱን ለማሳደግ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በደሴ ከተማ የከፈተ ሲሆን በሌሎች ከተሞች እና በአዲስ አበባም ቅርንጫፍ በመክፈት ተደራሽ ለመሆን እየሠራ የሚገኝ ተቋም ነው።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us