ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ዋና መስሪያ ቤቱን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በይፋ ስራ ያስጀምራል።
ማኀበሩ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ መነሻ ካፒታል ከፌደራል ኀብረት ስራ ኮሚሽን እውቅና በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ሀገራዊ ተቋም ነው።
የማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤትም በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ደምበል ወደ ጋዜቦ መንገድ አሚር ኮሜርሻል ኮምፕሌክስ ህንጻ ላይ ይገኛል።
በይፋዊ ስራ ማሥጀመሪያ ሥነ ስርዓቱም የፌደራል ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ተወካዮችን ጨምሮ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ የማኅበሩ ባለ ድርሻ አባላት፣ የማኀበሩ ስራ አመራር እና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአሁኑ ወቅት ማኀበሩ ከ750 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን የካፒታል መጠኑም ከ20 ሚሊየን ብር በላይ አድጓል።
ማኀበሩ ለመኪና፣ ለቤት መግዣ እንዲሁም ለሌሎች የቢዝነስ ሥራዎች እሥከ 4 ሚሊየን ብር ብድር እየሠጠ መሆኑም ተገልጿል።
ባለፈው የካቲት 30/2018 ዓ.ም በፌደራል ኀብረት ሥራ ኮሚሽን የምዝገባ ምሥክር ወረቀት የተሠጠው ማኀበሩ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ሥራዎችን መሥራቱንና ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልል ከተሞች ቅርንጫፍ እንደሚከፍት አስታውቋል።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ዋና መስሪያ ቤቱን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በይፋ ስራ ያስጀምራል።