በኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር በቢሮ ስነ ስርዓትና ፕሮቶኮል ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናውም የማህበሩ ሰራተኞች፣ የማኔጅመንት አባላትና የማኅበሩ አባላት የተሳተፉ ሲሆን ሰራተኞ የሚሰሩትን ስራ በቅልጥፍና እና በስነ ምግባር እንዲሁም ከደንበኞች ጋር ያላቸው ግንኙነት የተሳለጠ እንዲሆን ነው የስነ ስርዓትና ፕሮቶኮል ስልጠናው የተሰጠው፡፡
ስልጠናው በኃላፊና በባለሙያዉ እንዲሁም ወቅቱ የሚጠይቀውን እርስ በዕርስ የመከባበርና የመተባበር ግንኙነት መርህ በመከተል ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተጠቅሷል፡፡
ኢንፊኒቲ በተያዘው በጀት ዓመት ከፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን እውቅና በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራ የቁጠባ እና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ነው፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
በኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር በቢሮ ስነ ስርዓትና ፕሮቶኮል ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡