የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን በኢንፊኒቲ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ክትትልና ድጋፍ አደረገ፡፡
ከኮሚሽኑ የተወጣጡ የቁጠባና ፋይናንስ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካዮች፣ የቁጠባ፣ የወለድ አልባ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ /የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ነው የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን ያከናወነው፡፡
የኢንፊኒቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር እስማኤል ሀሰንን ጨምሮ የቁጥጥርና የብድር ኮሚቴ፣ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ የሰው ሀብት ልማት እና የእቅድ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በቁጠባ አሰባሰብ፣ በአባል ማፍራት፣ የሼር ሽያጭ እና የብድር አሰጣጥ ሂደቶችን በተመለከተ ነው ግምገማው የተካሄደው፡፡
ኢንፊኒቲ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበው ውጤት የሚበረታታና አርዓያነት ያለው መሆኑም የተጠቀሰ ሲሆን ማኅበሩ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን የበለጠ ለማጠናከር በኮሚሽኑ በኩል ሙያዊ፣ የቴክኒክና አቅም ግንባታ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተጠቁሟል፡፡
በማኅበሩ በኩል የተሻለ ለውጥ ለማስመዝገብና የአባላትን ጥቅም ለማሳደግ የኮሚሽኑ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ላደረጉት ድጋፍም ማኅበሩ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ህብረት ለዘላቂ ልማት!
የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን በኢንፊኒቲ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ክትትልና ድጋፍ አደረገ፡፡