ኢንፊኒቲ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ብድር መስጠቱን አስታወቀ።
( ኢንፊኒቲ፡ ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም)
የኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምና የማርኬቲንግ ሥትራቴጂ ዙሪያ ተወያይቷል።
የማኀበሩ ስራ አመራርና ማኔጅመንት እንዱሁም አባላት በተገኙበት በአዜማን ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት በማኀበሩ ቁጠባ እና ብድር አሰጣጥ እንዲሁም በአባላት ማፍራት ዙሪያ ሥኬታማ ሥራዎች መሠራታቸው ተጠቁሟል።
ማኀበሩ በዚሁ ሩብ ዓመት ለበርካታ ደንበኞቹ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን የሠራ ሲሆን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ብድር መሥጠቱም ተገልጿል።
የማኀበሩ ስራ አመራር ሰብሳቢ ዶ/ር እስማኤል ሐሰን በአጭር ጊዜ ለደንበኞቹ ብድር በመሥጠት አለኝታነቱን ያሣየው ማኀበሩ በቀጣይም ለበርካታ የኀብረተሠብ ክፍሎች በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎት ለመሥጠት እየሠራ ሥለመሆኑ አንሥተዋል።
በጊዜ ገደብ ቁጠባ ሥኬታማ ሥራ መሠራቱን ያነሡት የማኀበሩ ዋና ሥራ አስፈጸሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ በበኩላቸው ለብዙ ደንበኞች ብድር የተሠጠ ቢሆንም አሁንም ከሀያ በላይ የብድር ጥያቄ ያቀረቡ አባላትን ለማሥተናገድ በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል።
ደንበኞች ማኀበሩን በመቀላቀል ቢዝነስ ለመጀመርም ሆነ ለማስፋፋት፣ ለጤና፣ ለትምህርትና ለሌሎችም አገልግሎቶች ፈጣን የቁጠባ እና ብድር አገልግት ማግኘት እንደሚችሉም አቶ እስክንድር አስገንዝበዋል።
ማኀበሩ በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎት በመሥጠትና የማኀበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በዲጂታል ቴክኖሎጅ በመታገዝ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እንደሚሠራም በውይይቱ ተነስቷል።
ደንበኞች በቀላሉ በተቋሙ ድረ ገጽ www.infinitysaccos.com ላይ በመግባትና በመመዝገብ ባሉበት ሆነው አባል መሆንም ሆነ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም ተጠቁሟል።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ብድር መስጠቱን አስታወቀ።