ኢንፊኒቲ ለሌሎች ማኀበራት አርዐያ የሚሆን ተቋም ነው፡- የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለደንበኞቹ አስፈላጊውን የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት እየሠጠ መሆኑ ለሌሎችም አርዐያ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አምባዬ ወልዴ ገልጸዋል።
ማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤቱን በይፋ ባስጀመረበት ፕሮግራም ላይ የተገኙት ኃላፊው ባለፈው የካቲት 30/2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሠራ ምሥክር ወረቀት ከተሠጠበት ጊዜ አንሥቶ ያለው ጊዜ አጭር ቢሆንም አመርቂ ውጤት አሣይቷል ብለዋል።
ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሥራት የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የተናገሩት አቶ አምባዬ ይህንን ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኃላፊው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ኮሚሽኑም በሥልጠና፣ በአቅም ግንባታ እና በሌሎች አግባቦች ድጋፉን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ ለሌሎች ማኀበራት አርዐያ የሚሆን ተቋም ነው፡- የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን