ኢንፊኒቲ ዋና መሥሪያ ቤቱን በይፋ ስራ አስጀመረ።
.............
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ዋና መስሪያ ቤቱን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በይፋ ስራ አስጀምሯል።
የማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤትም በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ደምበል ወደ ጋዜቦ መንገድ አሚር ኮሜርሻል ኮምፕሌክስ ህንጻ ላይ ይገኛል።
በይፋዊ ስራ ማሥጀመሪያ ሥነ ስርዓቱም የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ የማኅበሩ ባለ ድርሻ አባላት፣ የማኀበሩ ስራ አመራር እና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ማኅበሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በብድር መኪና ለገዛላቸው ደንበኞቹ የመኪና ቁልፍ ርክክብ አካሂዷል፡፡ ደንበኞቹም በማኅበሩ በኩል የተደረገው የብድር አገልግሎት ፈጣንና ማህበሩን ተመራጭ ስለማድረጉ ገልጸዋል፡፡
ማኅበሩ ከንብ ባንክ፣ እንዲሁም ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/መሰራዊ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር እና ግርማ የመኪና አስመጭ ኩባንያ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ማኅበሩ አዲስ ያበለጸገውንና ደንበኞች ባሉበት በየትኛውም ቦታ ሆነው አባል መሆንና መቆጠብ እንዲሁም መበደር የሚችሉበትን እድል የያዘ ድረ ገጽ ማበልጸጉም በፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ማኀበሩ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ መነሻ ካፒታል ከፌደራል ኀብረት ስራ ኮሚሽን እውቅና በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ሀገራዊ ተቋም ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ750 በላይ አባላት እንዳሉትና የካፒታል መጠኑም ከ20 ሚሊየን ብር በላይ አድጓል።
ማኀበሩ ለመኪና፣ ለቤት መግዣ እንዲሁም ለሌሎች የቢዝነስ ሥራዎች እሥከ 4 ሚሊየን ብር ብድር እየሠጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ባለፈው የካቲት 30/2018 ዓ.ም በፌደራል ኀብረት ሥራ ኮሚሽን የምዝገባ ምሥክር ወረቀት የተሠጠው ማኀበሩ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ሥራዎችን መሥራቱንና ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልል ከተሞች ቅርንጫፍ እንደሚከፍት አስታውቋል።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ዋና መስሪያ ቤቱን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በይፋ ስራ አስጀምሯል።