ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ለደንበኞቹ የመኪና ቁልፍ አስረከበ።
ማኀበሩ የቀረቡለትን በርካታ የብድር ጥያቄዎች እየመለሠ ሲሆን የመኪና ብድር ለሠጣቸው ደንበኞቹም ቁልፍ ሰጥቷል፣
መኪናቸውን መረከባቸው ድርጅቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የገባውን ቃል በተግባር ማሳየቱንና ደንበኞቹን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ቁልፋቸውን የተረከቡ ደንበኞች ገልጸዋል፡፡
ማኅበሩ ለቤት፣ ለመኪና፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለቢዝነስና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚሰጠውን የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠሉንና ለወለድ አልባ አገልግሎትም ልዩ ትኩረት መስጠቱን የማኅበሩ ስራ አመራር ሰብሳቢ ዶክተር እስማኤል ሀሰን ገልጸዋል፡፡
ማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤቱን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በይፋ ስራ ያስጀመረ ሲሆን ዋና መስሪያ ቤትም በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ደምበል ወደ ጋዜቦ መንገድ አሚር ኮሜርሻል ኮምፕሌክስ ህንጻ ላይ ይገኛል።
በይፋዊ ስራ ማሥጀመሪያ ሥነ ስርዓቱም የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ የማኅበሩ ባለ ድርሻ አባላት፣ የማኀበሩ ስራ አመራር እና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ለደንበኞቹ የመኪና ቁልፍ አስረከበ።